የመክፈቻ መርሐግብር
ዓመታዊው የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት 2018 መክፈቻ መርሐግብር በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማ
ከጥቅምት 17 – 21፣ 2018 ፡ አገር አቀፍ ዘመቻ – መክፈቻ መርሐግብር በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማ

የ 2018 አገር አቀፉ ዓመታዊው የፋይናንስ ትምህርት ሳምንት ዘመቻ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተዘጋጀ ሲሆን በተባባሪነት በፋይናንስ ዘርፍ የሴቶች ጥምረት (NEWFin)፣ የተባበሩት መንግስታት ካፒታል ልማት ፈንድ(UNCDF) ሰዊፍት(SWIFT) ፕሮግራም የክልል መንግስታትና የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡ መሪ ቃሉ “የፋይናንስ ትምህርትን ማጎልበትና የደንበኞችን ጥበቃን ማጠናከር” ሲሆን ዋና ዓላማውም አገር አቀፉን የፋይናንስ ትምህርት ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ የወጣቶችን የፋይናንስ ደህንነት ማሳደግና በአገር አቀፍ ደረጃ የፋይናንስ ተደራሽትን ማስፋት ነው፡፡
የዚህ ዓመቱ ዘመቻ በዋናነት ትኩረት ያደረገው የሞባይል ገንዘብ ትምህርትና የደንበኞች ጥበቃ ላይ ሲሆን በዚህም ወደ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ ወጣቶችን ከነሱም ውስጥ ግማሽ የሚሆኑ ሴቶችን ማእከል አድርጓል፡፡ ለመድረስ የታቀደውም በማህበረሰብ አቀፍ ወርክሾፕ፣ በወጣቶች አቅም ግንባታ ፕሮግራም፣ የጎዳና ላይ ትዕይንቶች፣ በመገናኛ ብዙሀን በሚተላለፉ መልዕክቶችንና በፋይናንስ ተቋማት በሚካሄዱ የሂሳብ ማስከፈት ዘመቻዎች ነው፡፡
የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ በማድረግና የደንበኞች ጥበቃን በማሳደግ የ 2018 ዓመታዊው የፋይናንስ ትምህርት ሳምንት የፋይናንስ አካታችነትን በማጠናከርና የፋይናንስ ደንበኞችን ዕምነት በመገንባት እ.አ.አ በ 2030 ለመድረስ በታቀደው የፋይናንስ አካታችነት ግብ ላይ የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል፡፡
የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ የሆነችው ጋምቤላ የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት መክፈቻ ፕሮግራም እንዲካሄድባት የተመረጠችው በዋናነት የገጠሩም ሆነ የከተማው ነዋሪ መገናኛ ማዕከል ሆነ ስለምታገለግል ነው፡፡ ከተማዋ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም በርካታ የከተማዋና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ላይ የፋይናንስ ዕውቀት ውስንነት፣ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነት ላይ እንቅፋቶች እና በቂ የሆነ የፋይናንስ መረጃ አለማግኘት ይስተዋላል፡፡
የገጠሩን ማህበረሰብ የፋይናንስ ዕውቀት ማጎልበት የብሔራዊው ፋይናንስ ስትራቴጂ ዋና አካል ነው፡፡ ይህም ጋምቤላ ክልልን የፋይናንስ ግንዛቤ በመፍጠር፣ አካታችነትን በማጠናከርና የገጠሩን ማሕበረሰብ በመረጃ ላይ የተመሠረት ውሳኔ እንዲወስኑ በማስቻል ረገድ ዋነኛ መነሻ ያደርጋታል፡፡
ከጥቅምት 17 – 21፣ 2018 ፡ አገር አቀፍ ዘመቻ – መክፈቻ መርሃግብር በጋምቤላ ክልል
ዓመታዊው የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት 2018 መክፈቻ መርሐግብር በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማ
Financial literacy to rural communities and Female Employees’ Workshop
Workshop on Consumer Protection for Financial Institutions
School club sessions, teacher briefs, and entrepreneurship linkages for students.
Field Visits, Results Sharing and Media Coverage
የፋይናንስ ደንበኞች ጥበቃ
የማህበረሰብ አቀፍ ተሳትፎ
የፋይናንስ ትምህርት ለገጠሩ ማህበረሰብ
የሴት የፋይናንስ ተቋማት ሠራተኞች ወርክሾፕ
የጎዳና ላይ ትእይንት ዘመቻ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ላይ
ወጣቶች
ዓመታዊው የፋይናንስ ደንበኞች ሳምንት አስተባባሪ ቡድን