
አገር አቀፍ ዘመቻ
ዓመታዊው የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት 2018
የፋይናንስ ትምህርት ሳምንት በዋናነት የፋይናንስ ተቋማትን፣ የመንግስት አካላትንና የልማት ድርጅቶችን በጋራ በማገናኘት በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የፋይናንስ ትምህርት መልእክቶችን ያስተላልፋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በጾታ የተከፋፈለ መረጃ በማጠናከር ዘመቻው አካታች የሆነ የሚላካ በአገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ የሚሠጠው መሻሻልን ለማምጣት አልሟል፡፡ በዚህም ዘመቻው አገሪቱ በረጅም እቅድ የያዘችውን ጠንካራ፣ ለሁሉም ተደራሽና ፍትሀዊ የሆነ የፋይናንስ ሥርዓት የመገንባት ራዕይን ያግዛል፡፡
የጋምቤላ ክልል ለምን?
የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ የሆነችው ጋምቤላ የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት መክፈቻ ፕሮግራም እንዲካሄድባት የተመረጠችው በዋናነት የገጠሩም ሆነ የከተማው ነዋሪ መገናኛ ማዕከል ሆነ ስለምታገለግል ነው፡፡ ከተማዋ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም በርካታ የከተማዋና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ላይ የፋይናንስ ዕውቀት ውስንነት፣ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነት ላይ እንቅፋቶች እና በቂ የሆነ የፋይናንስ መረጃ አለማግኘት ይስተዋላል፡፡
የገጠሩን ማህበረሰብ የፋይናንስ ዕውቀት ማጎልበት የብሔራዊው ፋይናንስ ስትራቴጂ ዋና አካል ነው፡፡ ይህም ጋምቤላ ክልልን የፋይናንስ ግንዛቤ በመፍጠር፣ አካታችነትን በማጠናከርና የገጠሩን ማሕበረሰብ በመረጃ ላይ የተመሠረት ውሳኔ እንዲወስኑ በማስቻል ረገድ ዋነኛ መነሻ ያደርጋታል፡፡
ከጥቅምት 17 – 21፣ 2018 ፡ አገር አቀፍ ዘመቻ – መክፈቻ መርሃግብር በጋምቤላ ክልል
የዘመቻው ግቦች እና ዓላማዎች
የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት ቀጣይ መዳረሻዎች
ዋናዋና ተግባራት
የፋይናንስ ደንበኞች ጥበቃ
የማህበረሰብ አቀፍ ተሳትፎ
የፋይናንስ ትምህርት ለገጠሩ ማህበረሰብ
የሴት የፋይናንስ ተቋማት ሠራተኞች ወርክሾፕ
የጎዳና ላይ ትእይንት ዘመቻ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ላይ
ወጣቶች
በጾታ የተከፋፈለ መረጃ :
እሴትና ግቦች
በጾታ የተከፋፈለ መረጃ ለተለያዩ ቡድኖች የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ እንደሆነ ምንያህል ተጠቃሚና ትርፋማ እንደሆኑ ለመረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት መረጃ ከሌለ የፋይናንስ አካታችነት እቅስቃሴዎች የተወሰኑ የህብረሰተብ ክፍሎች ያሉባቸውን ችግሮች ያለመገንዘብ ስጋት ይፈጥራል፡፡
እንደዚህ አይነት መረጃዎችን መሰብሰብና መተንተን የፋይናንስ ተቋማት፣ ፖሊሲ አውጭዎችንና የልማት አጋሮችን
በ 2018 የፋይናንስ ትምህርት ሳምንት ላይ በጾታ ላይ የተመሠረተ መረጃ አሰባሰብን በማጉላት የተሳትፎ ሂደቶችን የሚታዩ፣ የሚለኩና በድርጊት የተሞሉ መሆናቸውን እናረጋግጣለን፡፡
ጾታን መሠረት ያደረገ መረጃ የመሰብሰቢያ ሥርዓተን በመዘርጋት የፋይናንስ ትምህርት ሳምንት፣
በመጨረሻ፣ የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንቱ ዓላማ የተሳተፉትን ብዛት መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ቡድኖች ተሞክሮና ፍላጎቶች የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ወደፊት እንዲመራ መረጃ ማቅረብ ነው፣ በብሔራዊው የፋይናንስ ትምህርት ስትራቴጂና በተጨማሪም የፋይናንስ ሴቶች ጥምረት በNEWFin በተቀመጠው ራዕይ መሠረት የተካተተና እና እውነተኛ ፋይናንስ ሥርዓትን ማሳደግ ነው፡፡




